company logo

የራዲዮ ፕሮግራም

arbegna foto 5-09-2004 264.JPG

የእርሶ ምርጫ

የወደፊት የኢትዮጵያን ዕድል የሚወሰነው?
 
arbegna foto 5-09-2004 280.JPG

Login FormContent View Hits : 292220
08-01-2007

 
06-01-2007

 
የ2007 ዓ/ምን አዲስ አመት በማስመልከት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

- ከአምባገነኖች የጭቆና ቀንበር ለመላቀቅ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ ለነፃነቱና ለመብቱ ሲታገል ለኖረውና የትግሉ ባለቤት ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፣

- በአርበኝነት ትግል በዱር ገደሉ ህይወታችሁን፣ ጉልበታችሁን፣ ጊዜያችሁንና ዕውቀታችሁን ሳትሰስቱ ለተቀደሰው ዓላማ በማበርከት ላይ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት፣

- ከአስከፊው የስደት ውጣ ውረድ ኑሮ ላይ በመቀነስ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በሞራል እና በሀሳብ የአርበኝነት ትግሉን በመደገፍ ላይ ለምትገኙ በውጭ የምትኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም

- ለወደፊቷ ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያ በጎ ምኞትን በማሰብ ትግሉን ያለመታከት በመደገፍ ላይ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ

እንኳን ለ2007 ዓ/ም አዲስ ዓመት አደረሳችሁ አደረሰን!

ታሪክ ራሱን ደግሞ፣ የሀገር ህልውና ዳግም አደጋ ላይ ወድቆ ኢትዮጵያችን ልጆቼ በማለት የአድኑኝ ጥሪዋን ማሰማት ከጀመረች እነሆ ዓመታትን አስቆጠረች።በየዕለቱ በወያኔ የሚገደለው፣ የሚታሰረው፣ የሚሰደደውና የሚደበደበው ሕዝብ ቁጥር በአሐዝ ለማስፈር አዳጋች እየሆነ መቷል። የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ግፍ፣ በደልና የሉዓላዊነት መደፈር ጉዳዮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቤቱን ያላንኳኳበት ሰው አለ ማለት ዘበት ነው።

ወቅቱ ለጠየቀው የሀገር አድን ጥሪ ምላሽ በመስጠት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የአርበኝነት ትግል ችቦውን በመለኮስ እንደ ሻማ በመቅለጥ ብርሃን እየሰጠ እንደሆነ ይታወቃል። የተለኮሰውም ችቦ ሳይጠፋ የታለመለት ግብ ድረስ እንዲዘልቅ የደምና የአጥንት መስዋዕትነት በቋሚነት እየተገበረ ይገኛል። በዚህም ብዙ ሀገርና ወገን አፍቃሪ ጓዶች ከጎናችን ወድቀዋል፤ እኛም የመስዋዕትነት ረድፍ ላይ ሆነን የአርበኝነት ተጋድሎውን በጽኑ ሀገራዊና ወገናዊ ፍቅር ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግረነዋል። አዎ! አዲስ የትግል ምዕራፍ! ለዓመታት ሲካሄድ የቆየውን የተበታተነ ትግል በመሰብሰብ የወያኔን አገዛዝ እድሜ ለማሳጠር የተደረገው እልህ አስጨራሽ ጉዞ ፍሬ አፍርቶ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7 የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ የውህደቱን መንገድ ጀምረነዋል። የፍሬውም ተቋዳሽ የምንሆነበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።

አዲስ መንፈስ፣ አዲስ ዕቅድና አዲስ ራዕይ የአዲስ አመት አንዱ መገለጫዎች ናቸው። እነዚህንም መገለጫዎች ወደ መሬት ለማውረድ የአዲስ ዓመት ውጥን ማዘጋጀት የተለመደ ሂደት ነው።በመሆኑም የመላ ኢትዮጵያዊ የ2007 ዓ/ም አዲስ ዓመት ተቀዳሚ ውጥን መሆን ያለበት የወያኔን አገዛዝ ለማስወገድ የበኩሉን አስተዋፆ ለማበረከት ቆርጦ መነሳት ነው። የዚህንም ተፈፃሚነት ለማረጋገጥ አንድም ወደ ትግሉ በመቀላቀል ሲሆን ሌላው ደግሞ በየጊዜው ለሚኖሩ ሕዝባዊ ጥሪዎች ባለ አቅም ሁሉ ምላሽ በመስጠት ትግሉን መደገፍ ነው። በመሆኑም በአዲሱ አመት ውጥናችን ውስጥ መካተት ያለባቸውን ነገሮች መካተታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

አዲሱ ዓመትም የድል ዘመን እንዲሆንልን በተባበረ ክንድ የወያኔን አምባገነናዊ አገዛዝ ለማስወገድ የተጀመረውን ሁለገብ የአርበኝነት የትጥቅ ትግል በመደገፍ ሁሉም ዜጋ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ጎን እንዲቆምየትግል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

አንድነት ኃይል ነው!!!

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር

መስከረም 2007 ዓ/ም

 
መግለጫ

 
press release

 
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ለወራት ያሰለጠናቸውን የአርበኛ ሰራዊት አስመረቀ

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አንግቦ የተነሳውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማዳን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ ለዓላማቸው ጽኑ የሆኑና በወታደራዊ የጦር ስልት ከጠላት ጦር የላቀ ሠራዊት በማፍራት በሰሜን ምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል በተለያዩ ቦታዎች በወያኔ ላይ በሚያካሂዳቸው ውጊያዎች በጠላት ጦር ላይ ከባድ ውድመትን እያስከተለ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዳሜ ነሐሴ 3 ቀን 2006 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ለወራት በሽምቅ ውጊያ የወታደራዊ ሳይንስና በፖለቲካ መስክ ያሰለጠናቸውን የአርበኛ ሠራዊት ማስመረቁትን በስፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን የድርጅቱን ማሰልጠኛ ሃላፊ ጠቅሶ ዘግቧል።

Read more...
 
የትግል ጥሪ በውጭ ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ

 
የትግል ጥሪ በውጭ ለመትኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ

የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔ የአፈና ቀንበር ስር ከወደቀ አንስቶ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በማህበራዊ ሕይወቱ እጅግ ወደከፋ አቅጣጫ እያመራ ይገኛል በተለይም የመንደር ፖለቲካው በኢትዮጵያዊያን መካከል ለመፍጠር እየተሞከረ ያለው ልዩነት ስርዓቱ እንዳሰበውና እንደሚፈልገው ገቢር አይሁን እንጂ አገዛዙ የለኮሰውን የጥፋት እሳት በአፋጣኝ ተረባርበን ካላጠፋነው ለወደፊት በኢትዮጵያዊነት ስሜት እና መንፈስ ላይ አደጋ የሚፈጥር ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አምባገነኑንና ጎጠኛዉን የወያኔ አገዛዝ ለማስወገድ ከፍተኛ መስዋአትነት ከፍሏል።

ድርጅታችን ለኢትዮጵያና ሕዝቧ ጥቅም ሲል ዳገት ቁልቁለቱን፣ ረሃብና ጥሙን፣ ውርጭ ቸነፈሩን የኔ ብሎ በመቀበል አጥንቱን በመከስከስ ደሙን በማፍሰስና መተኪያ የሌላት ውድ ህይወቱን በመክፈል ለአገሩና ለሕዝቡ ያለዉን ጥልቅ ፍቅር በተግባር አስመስክሯል ።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለለውጥ ትግሉ በሰላማዊ ሰልፍ ፣ በሻማ ማብራት፣ የወያኔን ድብቅ አጀንዳ የተለያዩ መንግስታት እንዲያውቁት በማድረግ፣ በማማከር፣በገንዘብ ወ.ዘ.ተ ድጋፍ በማድረግ ቀላል የማይባል ሚና ተወጥተዋል ።

ይህ የተቀደሰ የአርበኝነት ትግል በተደራጀ እና ወጥነት ባለው መልኩ እንዲከናወን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአቶ የዋርካው መንግስቱ የሚመራ የዓለም አቀፍ ኮሚቴ በጊዜያዊነት መቋቋሙን እያስታወቅን ኮሚቴው ግንኙነቱና አጠቃላይ የውጭ እንቅስቃሴዎቹ ከግንባሩ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ አርበኛ ኑርጀባ አሰፋ እውቅናና ምክክር ይሆናል ከዚህ አሰራር ውጭ የሚደረግ ማንኛውንም አይነት የውጭ እንቅስቃሴ ግን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን።

በተቋቋመው የዓለም አቀፍ ኮሚቴ ስር በመደራጀት መላው ዲያስፖራ የየበኩሉን ድርሻ በመወጣት ለስደት የዳረገውን የወያኔ አገዛዝ ለመታገል ነገ ሳይሆን ዛሬ ሊነሳ ይገባል።

አንድነት ሃይል ነው !

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር

ሐምሌ 14-2006 ዓ/ም

 

 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራ-አስኪያጅ ከነበሩትና የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን በቅርቡ ከተቀላቀሉት ከአቶ መኳንንት አበጀ ጌታሁን ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ ክፍል-2

 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራ-አስኪያጅ ከነበሩትና የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን በቅርቡ ከተቀላቀሉት ከአቶ መኳንንት አበጀ ጌታሁን ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ ክፍል-1

 

Search
Copy right @2014 arbegnochginbar